Menu Content/Inhalt
Home
Fund Missing from Harari Regional Office PDF Print E-mail
Tuesday, 09 September 2008
 
በተሾመ ንቁ

የሐረሪ የዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት በሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ባካሄደው ምርመራ ከፍተኛ የገንዘብ ጉድለት መኖሩን አረጋግጧል፡፡

የዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት የ2ዐዐዐ በጀት ዓመት ዓመታዊ ሪፖርቱ በክልሉ የጥሬ ገንዘብ ጉድለትና ብልጫ፣ ውዝፍ ሒሳብ፣ የገቢ ደረሰኝ ተቆርጦ በመዝገብ ያልተመዘገበና በማነስ የተመዘገበ እንዲሁም በመዝገብ ተመዝግቦ ወደ ሌጀር ያልተላለፈ ሒሳብ መኖሩን አረጋግጧል፡፡ በተጨማሪም የግዢ የውል ስምምነት ያልቀረበለት ሒሳብ፤ ኘሮፎርማ፣ ፋክቱር፣ ቃለጉባዔ ያልቀረበለት ሒሳብ መኖሩን ምርመራው አመልክቷል፡፡
 
የምርመራ ሪፖርቱ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ 4 ሚሊዮን 35ዐ ሺህ ብር የእርዳታና ብድር ሒሳብ ከእርዳታ ሰጪዎችና አበዳሪዎች ለክልሉ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ገቢ የሆነና ክፍያ የተፈፀመበት መረጃ፣ እንዲሁም ሴክተር መሥሪያ ቤቶች የአፈፃፀም ሒሳብ የሚያሳይ መረጃ እንዲሁም የአፈፃፀም ሪፖርታቸውን የሚገልፅ መረጃ በቢሮው ሳይገኝ መቅረቱን አስታውቋል፡፡

በንግድና ኢንዱስትሪ ከተማ ልማት ቢሮ ውስጥ 5 ሚሊዮን 74 ሺህ 969 ብር የገቢ ደረሰኝ ያልተቆረጠለት ሂሳብ መኖሩን ምርመራው አረጋግጧል፡፡ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ውስጥ 219 ሺህ 1ዐ8 ብር የባንክ፣ ስቴትመንት ላይ የተመለከተ ነገር ግን የባንክ ዲፖዚት አድቫይስ ያልቀረበለት ሂሳብ ተገኝቷል፡፡ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ 3 ሚሊዮን 354 ሺህ 516 ብር የባንክ ሂሳብ ማስታወቂያ የመሥሪያ ቤቱ ሂሳብ ማመዛዘኛ ሪፖርት በማነስ ተመዝግቦ ተገኝቷል፡፡

በምርመራው መሠረት በክልሉ የገቢ ደረሰኝ ተቆርጦለት በመዝገብ ያልተመዘገበ 440 ሺህ 952.93 ብር መኖሩን አመልክቷል፡፡ የ949 ሺህ 170.23 ብር የሚገመት ንብረት ከአምስት መሥሪያ ቤቶች ገቢ ስለመደረጉ የሚገልፅ መረጃ አለመኖሩን ምርመራው አመልክቷል፡፡ በ12 መሥሪያ ቤቶች በድምሩ 51 ሺህ 419.09 ብር የተከፋይ ገቢ ግብር ሳይቆርጥ የግዢና የአገልግሎት ክፍያ መፈፀሙ ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ በሦስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ 71 ሺህ ብር በላይ የውል ስምምነት ያልተገባለት ክፍያ መፈፀሙን ምርመራው አትቷል፡፡ ምርመራው በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ 888 ሺህ ብር የግዢ ጥያቄ ሳይቀርብ ክፍያ መፈፀሙን፣ 121 ሺህ ብር ኘሮፎርማ ሳይቀርብ ግዢ መፈፀሙን፣ የ130 ሺህ ብር ግዢ በጨረታ ኮሚቴ ሳይወሰን መፈፀሙን፣ 62 ሺህ ብር ፋክቱር ሳይቀርብ ክፍያ መፈፀሙንና 775 ሺህ ብር የወጪ ማስረጃ ቀርቦ በመዝገብ ያልተመዘገቡ ሒሳቦች መኖራቸውን አብራርቷል፡፡

በክልለ ሦስት መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የጨረታ ሂደትን ያልተከተለ ግዢ መፈፀሙን ምርመራው አስታውቋል፡፡ በክልሉ በጄንኤላ አካባቢ ቀበሌ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ከ29 ሺህ ብር በላይ ክፍያ ኃላፊ ሳያፀድቅ መፈፀሙን አመልክቷል፡፡

የኦዲተር መሥሪያ ቤቱ ምርመራ በክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ከተማ ልማት ቢሮ 292 ሺህ 443 ብር የጥሬ ገንዘብ ጉለት መገኘቱን አመልክቷል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በባህልና ቱሪዝምና ማስታወቂያ ቢሮ ገንዘብ ያዦች 83 ሺህ ብር በላይ የጥሬ ገንዘብ ጉለት መኖሩን አስታውቋል፡፡
Last Updated ( Tuesday, 09 September 2008 )
 
< Prev   Next >

Polls

What concerns you most?
 
site_1189_0005.jpg

Syndicate

Who's Online

We have 4 guests online